ኅዳር 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) እድሜያቸው ከ60 አመት በላይ የሆኑና ጡረታ የወጡ ነገር ግን የመስራት አቅም ያላቸው አረጋውያን በሙያቸው ተሰማርተው መስራት እንዲችሉ የሚያግዝ መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
አረጋውያን የአገልግሎት ጊዜያቸውን አጠናቀው ጡረታ በሚወጡበት ጊዜ በቤት ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ ለድባቴ እንዲሁም ለጥቃት የሚጋለጡበት እድል ሰፊ እንደሆነ የሚገልጹት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአረጋውያንና ቤተሰብ መሪ ስራ አስፈጻሚ ተስፋዬ ሮቤሌ፤ አረጋውያን ከጡረታ በኋላ በሚኖራቸው ጊዜ ተደራጅተው በሙያቸው በመስራት ራሳቸውን መጥቀም እንዲችሉ የሚያግዝ መመሪያ ባለመኖሩ መመሪያውን ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አብራርተዋል።
አደረጃጀት እና መስፈርቶቹን በተመለከተ መመሪያው ዝርዝር ሃሳቦች እንዳሉት የገለጹት መሪ ስራ አስፈጻሚው፤ አረጋውያንን ለመደገፍ ከሚያስችሉ ስራዎች መካከል የመመሪያው መውጣት ዋነኛው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለአረጋውያን የሚሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ በመሆኑ የግንዛቤ ክፍተቱን ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የተናገሩት አቶ ተስፋዬ፤ መመሪያው በሁለተኛው ሩብ አመት እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል።
መመሪያው አረጋውያንን ከስነልቦና ተጽዕኖ ከማላቀቅም ባለፈ ከጡረታ በኋላ የሚኖራቸውን ገቢና የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚረዳ ነው ተብሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ