ኅዳር 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማርና ሌሎች ተግባራትን በላቀ ደረጃ ለመፈፀምና ተወዳዳሪነቱን ለማስቀጠል ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ለመሸጋገር የሚያስችለውን ዝግጅት እያከናወነ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስታወቁ፡፡
ፕሬዚዳንቱ አስራት አጸደወይን (ዶ/ር)ዩኒቨርሲቲው ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር የሚያስችለውን 13 የሚደርሱ መመሪያዎችና ፖሊሲዎችን እያዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡
ስራውን በተሳለጠ ሁኔታ ለማከናወንም አንድ ዐብይና 13 ንኡሳን ኮሚቴዎች በማቋቋም ወደ ስራ የተገባ ሲሆን፤ ስትራቴጂክ ፕላን በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላትና ለዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ማቅረቡን ገልፀዋል፡፡
ስትራቴጂክ ፕላኑ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ህግ አውጪን፣ የተማሪዎች የመግቢያ ፖሊሲን፣ የኢንዶውመንትና የሪሶርስ ሞብላይዜሽ ፖሊሲ ማቋቋሚያ አዋጅና ደንቦችን ማካተቱን ጠቁመዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝነት የሽግግር ሂደት ልምድና ተሞክሮ ለመቀመር መቻሉን ጠቁመው፤ ሂደቱ በጥሩ የዝግጅት ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
የሽግግር ሂደቱን ለማገዝም የአሜሪካና የፈረንሳይ ኤምባሲዎች በዘርፉ ባለሙያዎች የታገዘ የስልጠናና የምክክር መድረኮችን በማዘጋጀት ድጋፍ እየሰጡ እንደሚገኙ አመልክተዋል።
በቀጣዩ ዓመት ወደ ራስ ገዝነት ከሚሸጋገሩ የአገሪቷ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ መሆኑን የገለፁት ፕሬዚዳንቱ፤ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች በስፋት በመከናወን ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ