ኅዳር 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና ተቋማት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ መግለጫዎችንና ዘገባዎችን ሲያወጡ ሀገር ውስጥ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን በምን መልኩ ሽፋን ይስጡት የሚለውን በተመለከተ በህግ ደረጃ የተቀመጠ ነገር እንደሌለ አስታውቋል፡፡
በኢትጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሰልጣን የሚዲያና ማስታወቂያ ክትትል መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዴሬሳ ተረፈ፤ ዘገባዉን የሃገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን እንዴት ይጠቀሙት የሚለዉ ህግ ባይኖረዉም ሃገራዊ ጥቅምን ማስቀድም እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡን የህግ ባለሙያው አቶ አቤኔዘር ጥሩአየው በበኩላቸው፤ በሁለት መልኩ ጉዳዩን መመልከት እንደሚቻል አንስተዋል ፤ይህም ብሔራዊ ጥቅምን የሚጻረሩ ከሆነ በሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በጉዳዩ ላይ ግልፅ መረጃን ከሚመለከተቻው አካላት በመወሰድ ሚዛናዊ ዘገባ መስራት እንደሚጠበቅና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማትም በቂ ምላሽ መስጠት እንዳለባቸዉ ተናግረዋል፡፡
የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ያላነሱትን በተለይም እንደ ሰብዓዊ መብቶች ፤ የትምህርት ተደራሽነትና ግጭቶች አከባቢ ያሉ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚሰራጩ ዘገባዎች ግን ከፍተኛ ጥንቃቄና ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ እንዲሰራጩ፤ እርማት የሚያስፈልጋቸዉም በሚመለከታቸዉ አካላት እርማት እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
የዉጭ ሃገራት ሚዲያዎች ስለ ኢትዮጵያ የሚያወጡትን መረጃ ሀገራዊ ጥቅምን ባስጠበቀ መልኩ መዘገብ እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን የሃገር ዉስጥ ተቋማት ለዉጭ ሚዲያዎች ከሚሰጡት መረጃ በፊት የሃገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃንን ሊያስቀድሙ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ