ኅዳር 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎች በትራንስፖርት ዘርፉ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር ሲያጋጥማቸው ወደ 94 17 በመደወል ቅሬታቸውን ያቀርቡ እንደነበር ይታወቃል፡፡
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ደምሰው ሌሊሳ የጥቆማ መስጫ ኮድ ቁጥሩ ከነችግሩም ቢሆን ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸው ሰልፍ በሚኖርባቸው አካባቢዎች ፤ ተሽከርካሪዎች መምጣት ባለባቸው ጊዜ ሳይመጡ ሲቀሩ ከተሳፋሪዎቹ ጥቆማ ያገኙበት እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
አሁን ላይ ግን በከተማው ውስጥ በሚሰሩ የልማት ስራዎች ምክንያት የት ቦታ እንደተቋረጠ ሳይታወቅ አገልግሎቱ ከተቋረጠ ከ2 ሳምንት በላይ እንደሆነው ዳይሬክተሩ አቶ ደምሰው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡ችግሩን ለመፍታትም ለኢትዮ-ቴሌኮም በደብዳቤ እንዳሳወቁና ኢትዮ ቴሌኮም የችግሩን ቦታ ለይቶ ምላሽ እስከሚሰጥበት ደርስ እየተጠባበቁ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለውም በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ፤ የስምሪት እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለማዘመን ቢሮው የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ቢሮው በቀጣይ የተቋረጠውን የጥቆማ መስጫ ቁጥር የማስተካከል ስራና የጥቆማ ስርዓቱን በማዘመን ለደንበኞች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ