“በጸጥታና ደህንነት ተቋማት ያከናወነው የሪፎርም ስራ ኢትዮጽያን የሚመጥንና ዘመን ተሻጋሪ ተቋማትን ለመገንባት ጠንካራ መሰረት የጣለ ነው። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ደግሞ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ነው። አየር ኃይሉ 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ባለበት በዚህ ወቅት  ”ጸሐይ 2 ” የተሰኘችና በአየር ኃይሉ የተሰራች አውሮፕላን ለበረራ ብቁ አድርጓል። አውሮፕላኗ ግዳጅን በብቃት መፈጸም የሚያስችል ቴክኖሎጂ የታጠቀች ናት። ይህም አየር ኃይሉ በ2030 በአፍሪካ ስመጥር አየር ኃይል ለመሆን  የያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ በትክክለኛ ጎዳና ላይ መሆኑን የሚያመላክት ነው።”  👉ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ