ኅዳር 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የነጭ ሪቫን (የጸረ-ጾታዊ ጥቃት) ቀን በሀገራችን ኢትዮጵያ ለ19ኛ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡
“የሴቷ ጥቃት የኔም ነው ዝም አልልም” በሚል መሪ ቃል ከህዳር 16 እስከ ታህሳስ 1 በኢትዮጵያ እየተከበረ መሆኑን ተከትሎ፤ ቀኑን ከማክበር ባለፈ በሃገራችን መልኩን እየቀያየረ እየተስፋፋ የመጣዉን ፆታዊ ጥቃት ለመቅረፍ ምን አይነት ስራዎች ሊሰሩ ይገባል ሲል መናኸሪያ ሬዲዮ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያ አቶ ቴዎድሮስ አዱኛን አነጋግሯል ።
እንደነዚህ አይነት ቀናት በሃገር ደረጃ ታስበው መከበራቸው የሚያመጡት በጎ ነገር አለ ፤ በተለይም ለጉዳዩ ትኩረት ለመስጠትና ህብረተሰቡን ግንዛቤ ከማስጨበጥ አንፃር ከፍተኛ ሚና እንዳለቸዉ ተናግረዋል፡፡
ቀኑን ከማክበር ባሻገር በጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሴቶችን ከተለያዩ ጉዳቶች ለመታደግ እና የሴቶች ጥቃትን እንደ ሃገር ለማስቆም ከህጉ በተጨማሪ ማህበረሰቡ በከፍተኛ ትኩረት ጥቃት አድራሹን የመቅጣትና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በመንፈግ እንዲሁም በማግለል ተገቢውን እርምጃ ሊወስድበት እንደሚገባም አመላክተዋል ። በተጨማሪም እንደ ሃገር ጾታዊ ጥቃትን የሚቃወም ትዉልድ ለመፍጠር ማህበረሰብ ላይ ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ፆታዊ ጥቃቶች ለበርካታ ስነ-ልቦናዊ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች መነሻ ናቸው የሚሉት የሴቶችና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ መላኩ ባዬ፤ ፆታን መሰረት ላደረጉ ግጭትና ጦርነቶች መነሻ ምክንያት ናቸው በማለት ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል የህጉም የህብረተሰቡም ርብርብ ወሳኝ ነው፤ ይህንን በማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በየአመቱ ቀኑን አስመልክቶ የንቅናቄ መርሃ-ግብር ይደረጋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በዋናነት በህብረተሰቡ ዘንድ የተዛባውን የስርአተ ፆታ አመለካከት ለመቅረፍ ግንዛቤ እያስጨበጠ እንደሚገኝ ጠቁመዋል ። በተለይም የፍትህ አካላት ተገቢውን ቅጣት እንዲቀጡ ከማድረግ ባሻገር የህግ ክፍቶችን ማስተካከል እና ማረም ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል ።
አክለውም ቀኑን ከማክበር ባለፈ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቀናቶቹ ከተጠናቀቁ በኋላ ሊሰሩ የሚገቡ ስራዎች ላይ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ዉይይት እና ምክረ ሃሳብ እንደሚኖር ገልጸዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ