ኅዳር 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመጪው ሁለት ሳምንት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ በይፋ እንደሚጀምር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
እስካሁን የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች በተለየ መልኩ የኦሮሚያ ክልሉ ሰፋ ያለ መሆኑን የሚናገሩት የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ፤ የምክክር ሂደቱ ሁሉን አካታች እና አሳታፊ፣ ተአማኒና ግልጽ የሆነ አሠራር እንዲኖረው ሰፊ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ አስታውቀዋል፡፡
ተሳፊዎችም ለሀገር አንድነት የሚበጁ ሃሳቦችን በማንሳት የሚመካከሩበት እንዲሁም የአጀንዳ ሃሳቦቻቸውን የሚያዘጋጁበት መድረክ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
በአጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ላይ የሲቪክ ማህበራትን ጨምሮ በክልሉ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማትና ከ7ሺህ በላይ ተወካዮች እንደሚሳተፉም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።
በክልሉ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በአጀንዳ ማሰባሰቡ ወቅት የደህንነት ስጋት እንዳይገጥም በክልሉ ከሚገኙ የፀጥታ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ የሚደረገው የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራ በየትኛው ቦታ መከናወን እንዳለበት በተያዘው ሳምንት የሚወሰን መሆኑን የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ተናግረዋል፡፡
የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት በ9 ክልልችና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች በ615 ወረዳዎች ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁን ባሳለፍነው ሳምንት ኮሚሽኑ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ