ኅዳር 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጠውን ፆታዊ ጥቃት ለማስቀረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች፤ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጥናት ሊያስጠና መሆኑን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
በመዲናዋ የሚስተዋለው ፆታዊ ጥቃት ለመስፋፋቱ ገደብ የለሽ የበይነ መረብ አጠቃቀም ሊሆን እንደሚችል የሚገልጹት የቢሮው የስርዓተ ፆታ ማካተትና ማስረፅ ዳይሬክተር ወ/ሮ በረከት በቀለ ሰፊ ጥናት የሚያስፈልገው በመሆኑ ጨረታ ሊወጣ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በመዲናዋ የሚስተዋለውን ፆታዊ ጥቃት ለማስቀረት አስቀድሞ መከላከል፤ ለጥቃት ምላሽ መስጠትና ቅንጅታዊ አሰራሮች ላይ በትኩረት እየተሰራበት እንደሆነ ዳይሬክተሯ ገልፀዋል፡፡
ቢሮ ችግሩን ለመቅረፍ ሚና አላቸው ካላቸው የሃይማኖት ተቋማት እና ከእድሮች ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን እንዲሁም ተቋማቱም ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የመገናኛ ብዙሃኑም ኃላፊነታውን በሚገባ እየተወጡ እንዳልሆነ የተናገሩት ኃላፊዋ፤ የህግ ክፍተቶችን ለማረም ከአዲስ አበባ ምክር ቤትና ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
እየተሻሻሉ ያሉ ህጎች ቢኖሩም ባለው ህግ ላይ የአፈፃፀም ክፍተት መኖሩንም ነው የጠቆሙት፡፡
በመዲናዋ ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶችና ህፃናት ማገገሚያ የሚሆኑ ሁለት ማዕከላት መኖራቸውን የቢሮው የስርዓተ ፆታ ማካተትና ማስረፅ ዳይሬክተር ወ/ሮ በረከት በቀለ ተናግረዋል፡፡
አለም አቀፍ የፀረ ፆታ ጥቃት ቀን ዘንድሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33 ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ “የሴቷ ጥቃት የኔም ነው ዝም አልልም” በሚል መሪ ቃል ከህዳር 16 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 16 ቀናት እየተከበረ ይገኛል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ