ኅዳር 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ለፌደራል መንግስት ለ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ የ582 ቢሊዮን ብር አፅድቋል፡፡
በሃገሪቱ ያሉ የንግድ እንቅስቃሴዎች እየተዳከሙ ባሉበት ወቅት በሦስት ወር ውስጥ ይህን ያህል ተጨማሪ በጀት መፈቀዱ አግባብነት እንደሌለው እና የህዝቡን የኢኮኖሚ አቅም እንደሚያዳክም የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
መንግስት ተጨማሪ በጀት የሚያስፈልገው ቢሆንም፤ ግማሽ አመት እንኳን ሳይሆነው ተጨማሪ በጀት መጠየቁ ተገቢነት እንደሌለው የሚናገሩት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶክተር አረጋ ሹመቴ መንግስት እቅዶቹን መለስ ብሎ ሊፈትሽ እንደሚገባና አሁንም የገቢው ምንጭ ግልፅ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
ብሄራዊ ባንክ የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት እየሰራ ቢሆንም በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል እየተወሰኑ ያሉ የበጀት ውሳኔዎች ለስራው እንቅፋት እንደሚፈጥሩበት የተናገሩት ደግሞ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ክቡር ገና ናቸው፡፡
አሁን ላይ እንደተጨማሪ የተጠየቀው የበጀት መጠን ከዚህ ቀደም ለአንድ ዓመት የሚመደብ በጀት እንደነበር ገልጸው፤ መንግስት በአሁኑ ወቅት ገቢ እና ወጪው እየተመጣጠነ እንዳልሆነና ይህም ዜጎችን ለተጨማሪ የኑሮ ውድነት እንደሚዳርግ ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ብድርና እርዳታ ከአለም ባንክና ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ፈንድ ያገኘችበት ወቅት መሆኑን የሚናገሩት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፤ ከተፈቀደው ተጨማሪ በጀት ውስጥ 280 ቢሊየኑን ከግብር ለመሰብሰብ እንደታቀደ ተናግረዋል፡፡
መንግስት ከአቅሙ በላይ ከሆነ ብቻ ከብሄራዊ ባንክ በወራት የሚመለስ ብድር የሚያገኝ መሆኑንና በአዲሱ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አሰራር መሰረት ከብሄራዊ ባንክ የረጅም ጊዜ ብድር እንደማያገኝ አንስተው፤ ከገቢ ብቻ ወጪ እንደሚሸፈን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አስታውቀዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ