ኅዳር 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚቀርብላቸው ድጋፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠንም ሆነ በዓይነት በመቀነሱ ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብዓዊ መብቶች አያያዝን የተመለከተ ሦስተኛ ዓመታዊ ሪፖርቱን ባወጣበት ወቅት ገልጿል።
መናኸሪያ ሬዲዮ ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ድጋፍን በሚመለከት የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንን ጠይቋል።
በአደጋ ወቅት እንዲሁም ከአደጋ በኋላ ለተጎጂ ዜጎች የተለያዩ ድጋፎችን ማድረግ የተቋሙ ሃላፊነት መሆኑን ያነሱት በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አለማየሁ ወጬቶ በተለያየ ምክንያት ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎችን ክልሎች በራሳቸው አቅም ድጋፍ የሚያደርጉበት አሰራር መኖሩን ተናግረዋል፡፡
ከክልሎች አቅም በላይ በሚሆንበት ጊዜ በፌደራል ደረጃ ተጨማሪ ድጋፎች እንደሚደረጉ በመግለጽ እስካሁን ባለው ሁኔታ ለተፈናቃዮች የሚደረግ ድጋፍ ቀንሷል የሚል ቅሬታ እንዳልመጣ እና ባለው መረጃ መሰረት አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎች እየተደረጉ እንዳለ ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን በአሰራር ስርአቶች የሚኖሩ ክፍተቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ አንስተዉ በክልል ከሚገኙና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ተፈናቃዮችን ወደ ቀደመ ቀያቸው የመመለስ ተግባር በትኩረት እየተሰራ ቢሆንም ወደ ቀያቸው የተመለሱ ተፈናቃዮች ወደ መጠለያ ካምፕ ተመልሶ መምጣት ተግዳሮት ሆኖ መቀጠሉን አንስተዋል፡፡
ስራ አስፈጻሚው በክልሎችና በፌዴራል መካከል ያለው ቅንጅታዊ አሠራር ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን በተመለከተም ከመቼውም ጊዜ በላይ ከክልሎች ጋር በመናበብ እየተሰራ እንዳለና ከዚህ ጋር ተያይዞ በየትኛውም አካል የሚቀርቡ ቅሬታዎችና የአሰራር ክፍተቶች እንደሚታዩም ገልጸዋል።
ለተፈናቃዮች እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ ቢገለጽም የተፈናቃዮችን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ በቂ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች ወቅቱን ጠብቀው ባለመቅረባቸው ሴቶችና ወጣቶች ራሳቸውን ለጥቃትና ለጉልበት ብዝበዛ ሊያጋልጡ የሚችሉ ሥራዎች ውስጥ እንዲሰማሩ መገደዳቸውን ኢሰመኮ በወጣው ሪፖርት ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ