ኅዳር 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ን እ.ኤ.አ ከ1980 እስከ 1991 ዓ.ም በዋና ስራ አስፈፃሚነት በማገልገል ለአየር መንገዱ ዘመን ተሻጋሪ ዕድገት የበኩላቸውን የመሪነት አስተዋፅዖ ያበረከቱት ካፒቴን መሐመድ አሕመድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ካፒቴን መሐመድ አሕመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ባገለገሉበት ወቅት አየር መንገዱ ዛሬ ለደረሰበት የስኬት ደረጃ እንዲበቃ መሰረት የጣሉ ውሳኔዎችን በማሳለፍ የማይተካ የመሪነት ሚናቸውን ተጫውተው አልፈዋል ሲል አየር መንገዱ ገልጿል፡፡
የካፒቴን መሐመድ አሕመድ ስርዐተ ቀብር ዛሬ ሕዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ፣ የቀድሞ የስራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በኮልፌ ሙስሊም መካነ መቃብር መፈጸሙ ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ