ኅዳር 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባው 582 ቢሊየን ብር ለፌደራል መንግስት ለ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት አድርጎ አፅድቋል፡፡
የፀደቀው ተጨማሪ በጀት ለውጭ እና ለሀገር ውስጥ ዕዳ ክፍያ፣ ለማህበራዊ በጀት ድጎማ (ለማዳበሪያ፣ ለመድሐኒት፣ ለምግብ ዘይትና ሌሎች)፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፋፊያ፣ ለማህበራዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም እና ለመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ማሻሻያ እንደሚውል ተመላክቷል፡፡
ተጨማሪ በጀቱ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያካሄደቸውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ተከትሎ ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ የሚገኘው በጀት በመጨመሩ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ለ2017 በጀት አመት ከቀረበው 582 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ውስጥ ለመደበኛ ወጪ 393 ቢሊየን ብር፣ ለካፒታል ወጪ 70 ቢሊየን ብር፣ ለወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ 119 ቢሊየን ብር ነው ተብሏል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ