ኅዳር 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቅርቡ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የ738 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር ብድር መፍቀዷ እና በገንዘቡም በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን የንግድ ትስስር ያጠናክራል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የመንገድ ፕሮጀክት እንደሚሰራ መገለጹ ይታወቃል፡፡
ፕሮጀክቱም በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መንገዶች ባለስልጣን የሚሰራ መሆኑም ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት እና የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ሲሳይ ደርቤ፤ በኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን መካከል ይገነባል የተባለው የመንገድ ፕሮጀክት ከፍተኛ ጥቅም እንደሚኖረው ተናግረዋል።
በመንገድ ፕሮጀክቱ የሚሳተፉ ስራ ተቋራጭ እና ባለሙያዎችን በተመለከተ በባለስልጣኑ የወጣ መስፈርት እንዳለ እና መስፈርቱን የሚያሟሉትም እንደሚሳተፉበት አስታውቀዋል፡፡
ከመስፈርቶቹ መካከል ስራ ተቋራጮቹ የሚኖራቸው ካፒታል፣ የሰው ሀይል፣ ልምድ፣ የበጀት አጠቃቀም፣ የስራ ጥራት፣ የጊዜ አጠቃቀም እንዲሁም ፕሮጀክቶችን የማስተዳደር አቅም ዋነኛ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ባለስልጣኑ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የስራ ተቋራጮች በፕሮጀክቱ እንዲሳተፉ ምቹ ሁኔታዎች የማመቻቸት፣ የህግ ማዕቀፎች ማውጣት፣ ተወዳዳሪ መሆን የሚችሉበትን አውድ የመፍጠር ስራ እንደሚሰራም ነው የተናገሩት፡፡
ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን የሚያስተሳስረው የመንገድ መሰረተ ልማት የሁለቱን አገራት የንግድ ትስስር የሚያሳልጥ እና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያመጣ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ፕሮጀክቱም የግንባታ ዘርፉን እንደሚያነቃቃው ነው የተመላከተው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ