ኅዳር 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከ20 ሚሊየን በላይ ወይም ከ17 በመቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን መንገድ ላይ እንደሚፀዳዱና የሃገሪቱን ገፅታ እያበላሸ መሆኑን ተከትሎ በአዋጅ መክልከል እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
ባለፉት ዘመናትም ድርጊቱን የሚከለክሉ መመሪያዎች ቢኖሩም አሁን ላለው ሁኔታ አስቻይ እንዳልሆኑና የሃገሪቱን ገፅታ የሚያበላሹ ተግባራት በመሆናቸው እስከ እስር የሚያደርስ ቅጣት መቅጣት የሚያስችል አዋጅ ለምክር ቤት ለማቅረብ እያተዘጋጀ መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የአካባቢ ጤና ፕሮግራም ዴስክ ሃላፊ አቶ አለሙ ቀጀላ ተናግረዋል፡፡
አዋጁን ለምክር ቤት ለማቅረብ በቅድሚያ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ማህበረሰቡ በመንገድ ላይ እንዲፀዳዳ እና ተያያዥ ችግሮች እንዲስተዋሉ ምክንያት እንደሚሆኑ የዴስክ ሃላፊ አቶ አለሙ ቀጀላ አክለው ተናግረዋል፡፡ ሁሉም የአገልግሎት መስጫ ተቋማት የመፀዳጃ ቤት ማስጠቀም ግዴታቸው ቢሆንም ይህን ሲደርጉ እንደማይስተዋል አመላክተዋል፡፡
በአንዳንድ ምግብ ቤቶች የሚስተዋለው የመፀዳጃ ቤት እና የማብሰያ ክፍል አጠገብ ለአጠገብ መሆን ሌላኛው ችግር እንደሆነ የገለጹት ኃላፊው፤ በንግድ ፍቃድ አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ክፍተት ይስተዋላል ብለዋል፡፡ አዲሱ አዋጅ ይህንንም እንደሚያካትት ተናግረዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ