ኅዳር 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዘንድሮውን ዓመት የኅዳር ጽዮን ክብረ በዓል በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ለማድረግ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።
የኅዳር ጽዮን ክብረ-በዓል ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በአክሱም ከተማ በደመቀ ሁኔታ የሚከበር ሲሆን ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች እንዲሁም ከውጭ ሃገራት የተወጣጡ ሰዎችም በአሉን ለማክበር ወደ ስፍራው የሚያቀኑ በመሆኑ ከወዲሁ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስተባባሪ አቶ ዘራዳይ ጸጋዬ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡
የሆቴል ማረፊያዎችንና የትራንስፖርት ሁኔታዎችን ምቹ የማደርግ እንዲሁም ታዳሚያን በዓሉን በሰላም አክብረው እንዲመለሱ ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶች በከተማው የሚገኙና በርካታ አመታትን ያስቆጠሩ ቅርሶችን እንዲሁም የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን ማስጎብኘት የጎዳና ላይ ዝግጅቶች እና የፓናል ውይይቶችን ጨምሮ ሌሎች ዝግጅቶች መኖራቸው የገለጹት አስተባባሪው ሃይማኖታዊና ባህላዊ ክብረ በዓላት የቱሪዝሙን ዘርፍ ብሎም ኢኮኖሚውን በማነቃቃት ረገድ የሚኖራቸው ፋይዳ የጎላ በመሆኑ በትኩረት እንደሚሰራበት ገልጸዋል።
በከተማው በድምቀት ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል የህዳር ጽዮን በዓል አንዱ ሲሆን በዓሉን በድምቀት ለማክበር የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑ ተገልጿል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ