ኅዳር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሁን ላይ እንደ ሀገር የምንከለተው የኢኮኖሚ ስርዓት አፈጻጸሙና መልኩ ካፒታሊስት ይምሰል እንጂ ቅይጥ ኢኮኖሚ፣ ካፒታሊስት ወይም ሌላም ተብሎ የሚሰየም ይህ ነው የሚባል ብያኔ እንደሌለው የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገልጿል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰሞኑን ከባለድርሻ አካላት ጋር ባካሄደው ጉባኤ ያለፉትን 60 ዓመታት የሀገሪቱን የምጣኔ ሃብት ጉዞ የቃኘ ሲሆን በተለይ አሁን የምንከተለው የምጣኔ ሃብት አማራጭ በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ፖሊሲ ላይ የሚመራ ቢሆንም እንደ ኢኮኖሚ ርእዮት ግን ስያሜ የተሰጠውና በልዩነት የሚታወቅ አንድ ማጠንጠኛ እንደሌለው የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገልጸዋል።
አሁን ላይ የመንግስት ምጣኔ ሃብታዊ አቋም በችግሮች ላይ የተመሰረተ ፖሊሲና መርህን መከተልና ማስፈጸም እንጂ ኢኮኖሚው ምን አይነት ስም ያለው ርእዮተ አለም ይከተል የሚለው አይደለም ሲሉ ዶክተር ፍጹም ተናግረዋል።
ከለውጡ በኋላ ላለፉት 6 ዓመታት የተሞከረውና የሚሞከረውም ይሄው ነው ያሉት ሚኒስትሯ፤ በተለይ ሀገር በቀል ኢኮኖሚው ግቡን እንዲመታ የባለድርሻ አካላት ተግባራዊ ልምምድና ጥናትም አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።
ፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጥሪ ያደረገላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች፣ የሙያ ማህበራትና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት ያለፉትን 60 አመታት የሀገሪቱን የምጣኔ ሃብት ጉዞና አሁናዊ የለውጥ ሂደቶችን በሚመለከት ከህዳር 10 እስከ ህዳር 12/2017 ዓ.ም ድረስ ጉባኤ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ