ኅዳር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለመጀመሪያ ጊዜ በሃገራችን እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ከተለያዩ ሃገራት የተወጣጡና በዘርፉ ያሉ ባለድርሻ አካላት ከኢንተርኔት አስተዳደር፤ ከሳይበር ወንጀልና ደህንነት እንዲሁም ከወደፊት የአፍሪካ ዲጂታል ራዕይ ጋር በተያያዘ ውይይት የሚደረግበት መድረክ መሆኑ ተገልጿል።
በጉባኤው በዲጂታሉ አለም ሊኖሩ የሚገቡ ህጎችን እና ከዚህ ጋር በተያያዘ ያለው አጠቃቀም ላይ ውይይቶች መደረጋቸውን የገለጹት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ስዩም መንገሻ ከኢንተርኔት አስተዳደር ጋር በተያያዘ የጸደቁ ህጎችን እንዲሁም በቀጣይ ለሚወጡ ህግና ፖሊሲዎች አጋዥ የሚሆኑ ሃሳቦች በጉባኤው መነሳታቸውን ተናግረዋል።
እየተስፋፋ ያለውን የዲጂታል አለም ተከትሎ በሚታዩ የኢንተርኔት አጠቃቀም ክፍተቶች ዙሪያ በቀጣይ መሰራት ስላለባቸው ጉዳዮች የተለያዩ ሃሳቦች የተነሱበት መድረክ መሆኑንም ገልጸዋል።
በጉባኤው በዲጂታሉ አለም አፍሪካን አንድ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያሉ ተግዳሮቶች የተለዩ ሲሆን ይህንን ለማሳካት የኢንተርኔት ተደራሽነትና ጥራት ለማሻሻል የሚረዱ እና የልምድ ልውውጦች ለማድረግ የሚያስችሉ መሰል መድረኮች መዘጋጀታቸው በዘርፉ ያሉ ስራዎችን ለማጠናከር ካላቸው ጠቀሜታ በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑንም ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።
የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤው በዛሬው እለት እንደሚጠናቀቅ የተገለጸ ሲሆን በቀጣይ ጊዜያት የሚካሄዱ መሰል መድረኮች ስለመኖራቸውም ተጠቁሟል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ