ኅዳር 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የህወሃት ክፍፍል በተሃድሶ ኮሚሽን ስራ ላይ መሰረታዊ እክል ሊፈጥር ይችላል የሚል ግምት እንደሌለው ብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የመጀመሪያ ዙር ተሃድሶ ስልጠና በትግራይ ክልል መጀመሩን በማስመለከት በሰጠው ጋዜጣዊ መገለጫ ወቅት አስታውቋል፡፡
ብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ቀጣይ ሳምንት በትግራይ ክልል ለሚገኙ 75 ሺህ ትጥቅ ለፈቱ የቀድሞ ተዋጊዎች የተሃድሶ ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡
በወቅቱም ከጋዜጠኞች አሁን ላይ በህወሃት መካከል እየተፈጠረ ያለው መከፋፈል ስራው ላይ እንቅፋት አይሆንም ወይ ተብሎ ለቀረበ ጥያቅ ምላሽ የሰጡት የትግራይ ክልል ተወካይ የብሄራዊ ተሃድሶ ምክትል ኮሚሽነር ተስፋዓለም ይህደጎ እክል የሚፈጥር ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡
አሁን ላይ ህወሃትን ያጋጠመው የመከፋፈል ችግር በራሱ ህወሃት እና በፌዴራል መንግስት በኩል እልባት ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅና በብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ስራው ላይም መሰረታዊ ችግር የሚፈጥር ነገር አለመኖሩን አስረግጠዉ ተናግረዋል፡፡
ትጥቅ ከመፍታት ጋር ተያይዞ ያለውን ነበራዊ ሁኔታ በተመለከተ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የመከላከያ ሚኒስቴር ተወካይ በኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጀኔራል ደርቤ መኩሪያ በበኩላቸው፤ የቀድሞ ታዋጊዎች ወደ ካምፕ ከገቡ በኋላ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም ከክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ጋር በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በበኩላቸው የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የቆይታ ጊዜ እየተጠናቀቀ ቢሆንም አሁንም በርካታ ስራዎች ከኮሚሽኑ እንደሚጠብቅ ከግምት ውስጥ በማስገባት የቆይታ ጊዜው ምክር ቤቱ ያራዝማል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
አሁን ላይ በስድስት ክልሎች ከ317 ሺህ በላይ የቀድሞ ታዋጊዎች በኮሚሽኑ በኩል ተለይተው የተሃድሶ ስልጠና ለመውሰድ በዝግጀት ላይ መሆናቸዉ ተመላክ
ምላሽ ይስጡ