ኅዳር 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በመዲናዋ በሚከሰቱ ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች የሰዎችን ህይወት መጥፋቱን እና ንብረትም መውደሙን ገልጾ ኮሚሽኑ በአሁኑ ሰዓት በህንጻዎች ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን መቀነስ የሚቻልበትን መመሪያ ወደ ስራ እንዳስገባ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል፡፡
እንደ ባለሙያው ገለጻ በህንጻ ስር የተገጠሙት መሳሪያዎች ለሚከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ቢሆንም አብዛኞቹ ከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ህንጻዎች የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎችን እንደማያስገጥሙ ገልጸዋል፡፡
ባለሙያው አያይዘውም ከዚህ ቀደም ይህ አይነቱን አደጋ መቀነስ እንዲቻል የራሱ ህግ ወጥቶለት የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ማስፈጸሚያ መመሪያ በተያዘው ህዳር ወር ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቀዋል፤
ባለሙያው አሁን ላይ የወጣው መመሪያው በህንጻዎች ላይ አደጋ ቢከሰት ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት የሚችል ነው ብለዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ