ኅዳር 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከዚህ ቀደም ባለንብረቶች ከተለያዩ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ቀድመው ይጠቀሙበት በነበረው የሰሌዳ ቁጥር ይሰሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በተሻሻለው የከተማዋ አሰራር ባለንብረቶቹ የመዲናዋ ነዋሪነታቸውን ካላረጋገጡ ተንቀሳቅሰው መስራት እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ የባጃጅ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ፍላጎት እንደሌለው የሚናገሩት የቢሮ ሃላፊ አቶ ያብባል አዲስ፤ ባለንብረቱ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪና የከተማዋ ነዋሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ መታወቂያ እንዲሁም በማህበር የተደራጀ ሊሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡
በባጃጅ ትራንስፖርት አማካኝነት በአዲስ አበባ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለማስቀረት ሲባል ውሳኔው መተላለፉን የሚያነሱት ሃላፊው የአዲስ አበባ የሰሌዳ ቁጥር ለማወጣት ተያያዥ ሌሎች መስፈርቶች መኖራቸውን እንዲሁም ከዚህ ቀደም የባጃጅ ትራንስፖርት የነበረባቸውና በአሁኑ ሰዓት የተቋረጠባቸው ቦታዎች ላይ አማራጭ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ለማስተካከል እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ላለፉት ወራት በመዲናዋ መስፈርቱን የማያሟሉ ባጃጆች እንዳይንቀሳቀሱ ታግደው እንደነበር የሚናገሩት ሃላፊው እስካሁን ወደ 1ሺህ 8 መቶ ባጃጆች መስፈሩት አሟልተው መስመር ተሰቷቸው ወደ ስራ መግባታቸውን አመላክተዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ