ኅዳር 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በሆቴልና መሰል ተቋማት የባለሙያዎችን አለባበስ በተመለከተ ከ50 ሺሕ እስከ 1 ሺሕ ብር የሚያስቀጣ ደንብ በካቢኔ አባላቱ ማጸደቁን አስታወቀ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በካቢኔ አባላቱ ውሳኔ መሰረት በደንብ ቁጥር 178/2016 መስረት ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት፤ የሰራተኛ የአለባበስ ሁኔታ የተመለከተ ድንብ ማጽደቁንና በደንቡ መሰረትም የሰራተኛ የአለባበስ ሁኔታ የማያስተካክሉ ከሆነ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፤ የብር የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድን እስከማገድ ድረስ የሚደርስ ቅጣትን በውስጡ አካቶ እንደያዘ የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ምክትል ቢሮ ሃ አቶ ሃፍታይ ገ/እግዚአብሄር ገልጸዋል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ በተደረገ የአሰሳ ስራ በሆቴሎች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ስራተኞች የሚለብሱት የአለባበስ ሁኔታ ከ98 በመቶ በላይ የሚሆኑት በረሳቸው ፈቃድ ወይም በፍላጎታቸው እንዳልሆነ ማየት ተችሏል ያሉት ምክትለ ቢሮ ሃላፊው አቶ ሃፍታይ፤የሰራተኛዉን መብት ከማስከበር ባሻገር ሃገራችን አለፍ ሲልም አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን ባህላችንን እሴት እና ማንነታችንን ማስጠበቅ ይገባልም ብለዋል፡፡
የቅጣት ሁኔታን በዝርዝር ያስረዱት በቱሪዝም ቢሮው የቱሪስት አግልግሎት ደረጃ ምደባ አቅም ግንባታ ስልጠና ባለሙያ ወ/ሮ ውቢት ስዩም፤ ደንቡ በከተማዋ ውስጥ ከከፍተኛ ሆቴል እና ሬስቶራንቶች እስከ የጀበና ቡና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ድረስ የቅጣት መጠኑ ይለያይ እንጂ ደንቡ ተፈጻሚ እንደሚደረግ አመላክተዋል፡፡
የቅጣት ሁኔታውም ደረጃ ’’ሀ’’ ’’ለ’’ እና ሐ ተብሎ እንደሚወሰን የገለጹት ባለሙያዋ በደረጃ ’ሀ’ የሚቀጡት 50 ሺሕ ብር፤ በደረጃ ’ለ’ የሚቀጡት 30ሺሕ ብር እንዲሁም በደረጃ ’ሐ’ የሚቀጡት ደግሞ 5ሺሕ ብር እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አለባበስን፤ የጸጉር አሰራርንና አጠቃላይ ኢትዮጵያዊነትን የሚመስሉ ጉዳዮችን ለደንበኞቻቸው በማስተጋባት በባህሉ በእሴቱና በማንነቱ የሚኮራ ትውልድን መገንባት እንደሚገባቸው ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ