ኅዳር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የተለያየ ሃሳብ እና አቋም ያላቸው ከ60 በላይ የሚሆኑ ሃገርና ክልል አቀፍ የፖለቲካ ፓርዎችን በውስጡ በመያዝ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተናጠል እና በጋራ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎችን ለማገዝ፤ በፖለቲካ ፓርቲዎች እና በመንግስት መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንዲፈጠር ለማድረግ የተቋቋመ ምክር ቤት እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ይህን ተከትሎም የፖለቲካ ፓርቲዎችን የአመራር አቅምን ለማሳደግ ያለመ የመግባቢያ ስምምነት ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር መፈራረሙን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገልጿል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የኮሙኒኬሽን እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዘዉዱ አለምነው የመግባቢያ ስምምነቱ የሃገር ሃብትን በጋራ በማስተዳደር ከብክነት ለማዳንና እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለዉን የፖለቲካ ሁኔታ ለመፍታት ቁልፍ የሆኑ ጥናትና ምርምሮችን ለማካሄድ ያለመ ነው ብለዋል፡፡
ባሁኑ ጊዜ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት በካቢኔ ደረጃ ገብተው ለሃገር እንዲያገለግሉ በመንግስት የተቀመጠዉን አቅጣጫ ለማገዝ ስምምነቱ ይረዳል ያሉት አቶ ዘውዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችን ብቻ ሳይሆን በጋራ ምክር ቤቱ ውስጥ የሚገኙ አመራሮችን አቅም ለማጎልበት የሚረዱ ሰነዶችን በጋራ ማዘጋጀት እንዲሁም ብቁ የሆኑ የፖለቲካ አመራሮችን በመለየት እውቅና የመስጠት አላማ እንዳለዉም ገልጸዋል፡፡
ይህ የመግባቢያ ስምምነት ለፓርቲዎች ምን ጥቅም ይኖረዋል በማለት ጣቢያችን ያነጋገራቸው የእናት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ጌትነት ወርቁ የፓርቲዎችን አቅም ማሳደግ፣ እርስ በርስ ግንኙነትን እንዲያሻሽሉ፣ የፖለቲካ ምህዳሩ ላይ ተፅዕኖ መፍጠር እንዲችሉ መርዳት የጋራ ምክር ቤቱ ሀላፊነት መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህ ስልጠና ለፓርቲ አመራሮች መሠጠቱ መልካም ጅማሮ ነው ብለዋል፡፡
ከሁለቱ ተቋማት የተወጣቱ የቴክኒክ ኮሚቴዎች ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት የመግባቢያ ስምምነቱ በአንድ ወር ውስጥ ወደ ትግበራ እንደሚገባ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካደሚ የኮሙኒኬሽን እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ