ኅዳር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የደቡብ አሜሪካ ሀገራት የ2026ቱ የአለም ዋንጫ ጋር ማጣሪያ ጨዋታዎች እያከናወኑ እንደሚገኙ ይታወቃል። ታዲያ ምክሲኮ በሁንዱራስ 2-0 በሆነ ውጤት ትላንት መሸነፏ አይዘነጋም።
ሁለቱንም ጎሎች ልዊስ ፓልማ ነው ያስቆጠረው ታዲያ ጨዋታወው ከተጠናቀቀ በኋላ ሁሌም እንደሚደረገው አሰልጣኞች በሚጨባበጡበት ጊዜ ላይ ማለትም የሁንዱራሱ አሰልጣኝ ሬይናልዶ ሩዌዳ ከሜክሲኮው አሰልጣኝ ሀቪዬር አጊዬር ጋር ሊጨባበጡ ሲሉ ከደጋፊዎች በተወረወረ የቢራ ጠርሙስ እና ሌሎች ቁሶች አሰልጣኙ ሀቪዬር አጊዬርን ፈንክተውታል።
ወዲያው ደም በደም ሆኖ ሜዳ ላይ ታይቷል። በመልበሻ ክፍል ደሙን በማስቆም የድህረ ጨዋታ መግለጫ ቢሰጥም አሁንም ደሙ በግንባሩ ሲዥጎደጎድ ተስተውሏል።
ምንም አይደለም ሲል ነው ሀሳብ የሰጠው ፤ እግርኳስ ነው ምንም ማለት አይደለም እነሱ ማሸነፍ ይገባቸዋል እንኳን ደስ አላችሁ ብያለሁ ሲል ሀሳብ የሰጠ ሲሆን ከዛ በኋላ ስለተፈጠረው ክስተት ግን ብዙ መናገር አልፈለገም። ብዙ መናገር አያስፈልግም ፤ እግር ኳስ ነው ያለ ነው ግን ለውጤቱ ተጠያቂው እኔ አይደለሁም ሲል ብቻ ተናግሯል።
የሜክሲኮ ደጋፊዎች ራሱን ሰለባ ያደረገው ራሱ ነው መሸነፋችን ሳያንስ ተዝናንቶ የተሻራኒ ቡድን አሰልጣኝ እንዴት ሰላም ይላል የሚለው የመፈናከታቸው መንስኤ ነው እያሉ ይገኛሉ። ጉዳዩ ግን መነጋገሪያ መሆኑን ቀጥሏል።
ምላሽ ይስጡ