ኅዳር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይፋዊ ንግግሮችን በወኪሉ አማካኝነት ከክለቡ ጋር መጀመሩ ሲገለጽ መቆየቱ አይዘነጋም።
ጎል ማስቆጠርን እና የሚያገኛቸውም እድሎች በሚገባ መጠቀምን ከፍ ባለ መልኩ የሚያዘወትረው የአጥቂ መስመር ተጫዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በኤቲሀድ ስቴዲየም የሚያቆየውን ውል ለማራዘም ከስምምነት ላይ ለመድረስ ስለመቃረቡ ተገልጿል።
በውሉ ላይ ሁለት አመት ታኩል ነው የሚቀረው ቢሆንም ግን ሲቲዎች ከወዲሁ የተጫዋቹን ውል ለማደስ እየሞከሩ ይገኛሉ። ያው መጠነኛ እክሎች ቢያጋጥማቸውም አሁን ከስምምነት ላይ ለመድረስ የተቃረቡ ይመስላል።
ኤርሊንግ ሀላንድ በፈረንጆቹ እስከ 2027 ከሲቲ ጋር የሚያቆየው ውል አለው ቢሆንም ተጫዋቹ ካለው አቅም እና ክህሎት ጋር በተያያዘ ተጫዋቹን ለማስፈረም የሚያንዣብቡ ክለቦች መኖራቸው ስለማይቀር ከወዲሁ ተጫዋቹን በአዲስ ውል ለማሰር ክለቡ መጠነ ሰፊ ስራዎችኝ በመስራት ከወኪሉ ራፋኤላ ፒሜንታ ጋር ንግግሮችን መጀመራቸው መገለፁ አይዘነጋም አሁን ታዲያ ከስምምነት ላይ ለመድረስ ስለመቃረባቸው ተገልጿል።
ማርካ እንደዘገበው ከሆነ ማንቸስተር ሲቲዎች በአዲሱ ውል ኤርሊንግ ሀላንድን የክለቡ ውድ ተከፋይ ተጫዋች የሚሆንበትን መንገድ በመዘርጋት ተጫዋቹን በኤቲሀድ የማቆየት ሀሳብ ነው ያላቸው። በአዲሱ ውሉ 500 ሺ ሳምንታዊ ክፍያ የሚያገኝ ይሆናል ተብሏል።
እንደሚታወቀው እዚ እለቡ ውስጥ ውዱ ሳምንታዊ ተከፋይ ተጫዋች ኬቨን ዲብሩይነ ሲሆኝ 425,000 ፓውንድ በሳምንት እንደሚያገኝ ይታወቃል። ሀላንድ ፊርማውን ሲያሰሰቀምጥ በሊጉ ብቻም ሳይሆን በአውሮፓ ውስጥ ከሚገኙ ከፍተኛ ተከፋይ ተጫዋቾች መካከል ፍራንኪ ዲዮንግን በመከተል ሁለተኛ ቦታ ላይ እንዲቀመጥ ያስችለዋል።
በአዲሱ ውል ግን ሀላንድ ከስፖንሰርሺግ እና ተያያዥ ጥቅማጥቅሞችን ጨምሮ በሳምንት 850,000 ፓውንድ የሚያገኝበት እድል እንደሚኖር ተጠቁሟል። ከዚሁ ጎን ለጎን ተጫዋቹ በአዲሱ ውሉ የውል ማፍረሻ እንዲካተትለት ይፈልጋል ዋናው ምክንያት ደግሞ የወደፊት የእግርኳስ ህይወቱን አቅጣጫ የማስቀመጡን ስልጣን በእጁ ለማስገባች በማሰብ መሆኑ ተገልጿል።
በአዲሱ ውሉ እስከ 2028-29 የውድድር ዘመን በሲቲ የሚያቆየው ሲሆን የውል ማፍረሻው ላይ ግን እስካሁን የተጫዋቹ ወኪል እና ክለቡ እየተነጋገሩ ይገኛሉ ተብሏል። ሲቲዎች የተጫዋቹ ውል ማፍረሻ 150 ሚሊዮን እንዲሆን ፍላጎት አላቸው። ተጫዋቹ ግን ይህ እንዲሆን ፍላጎት አለው።
የ24 አመቱ ኖርዌያዊ በ2022 ሀምሌ ወር ላይ ዶርትሙንድን ለቆ በ60 ሚሊዮን ፓውንድ ሲቲን ከተቀላቀለ በኋላ አስደናቂ ጊዜን ነው እያሳለፈ የሚገኘው በ102 ጨዋታዎች 97 ጎሎችን አስቆጥሯል። ክለቡ ውስጥ በነበረው የሁለት አመት ቆይታ ደግሞ 2 የፕሪሚየር ሊግ እንዲሁም ፤ 1 የሻምፒዮንስ ሊግ እንዲሁም 1 የFA ካፕ የዋንጫ ክብርን ማሳካትም ችሏል።
ምላሽ ይስጡ