ኅዳር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጸረ-ተህዋሲያን መድሃኒት አቅርቦት ችግር መኖሩን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
ለጸረ-ተህዋሲያን የሚሆኑ መድሃኒቶች ከድህረ ኮቪድ 19 በኋላ ምርቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ቀንሷል በማለት እንደ ሀገርም በኢትዮጵያም ምርቱ ባለመኖሩ የአቅርቦት ችግሩ መቀጠሉን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የመድሃኒትና የህክምና መሳሪያ አቅርቦት አገልግሎት ሃላፊ አቶ ሰይፈ ደምሴ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
እንደ ሀገር በፊት ከነበረው የ8 በመቶ አቅርቦት ወደ 36 በመቶ ከፍ ቢልም አሁንም ካለው ከፍተኛ ፍላጎት አንጻር የጸረ-ተህዋሲያን መድሃኒት በከፍተኛ ደረጃ እጥረት መኖሩን ገልጸዋል።
እንደ ሀገር መድሃኒቶቹን አምራች ካለመሆናችን በተጨማሪ የአለም አቀፍ የመድሃኒት የግዢ ስርዓቱና ምንዛሬውም ከፍተኛ ጫና ሆኖ በመቆየቱ ለአቅርቦት እጥረቱ ተጨማሪ ምክንያት መሆኑን ሃላፊው ተናግረዋል።
መንግስት የመድሃኒት አቅርቦት ሰልሰለቱን ለመቆጣጠርና ጤናማ ለማድረግ እየሰራ ቢሆንም ለጊዜው እጥረቱ መቀጠሉን ነው ሃላፊው ያብራሩት።
በጤናው ዘርፍ የተሻሻሉት ፖሊሲዎች ችግሩን ይቀንሳሉ ወይም የመጨረሻ መፍትሄ ይሆናሉ በሚል እየተሰራበት እንዳለ የገለጹት የቢሮው የዘርፉ ሃላፊ፤ የፍላጎት እና አቅርቦት አለመመጣጠን ችግሩን እንዳሰፋው ተናግረዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ