ኅዳር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአለም አትሌቲክስ እና ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የአበረታች ቅመምች (doping)ህግ ጥሰት በፈፀሙ አትሌቶች ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ።
አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ ፣ አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን እና አትሌት ህብስት ጥላሁን አስረስ የአበረታች ቅመሞች ህግ ጥሰት የፈፀሙ መሆኑ ተረጋግጧል ሲል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አስታውቋል።
በዚህም መሠረት፦
1.አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ እ.ኤ.አ February 29/2023 በተካሄደው ምርመራ ኢፒኦ (EPO) የተባለውን የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሙ በመረጋገጡ ለ 2 ዓመታት (እ.ኤ.አ ከApril 17/2024-April 16/2026 በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳይሳተፍ ቅጣት ተጥሎበታል፡፡
- አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን በተደረገላት የአትሌት ባይሎጂካል ፖስፖርት (ABP) ምርመራ አበረታች ቅመም መጠቀሟ የተረጋገጠ ሲሆን እ.ኤ.አ ከNovember 30/2023-November 29/2027 ለ4 ዓመታት በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳትሳተፍ ቅጣት ተጥሎባታል።
3.አትሌት ህብስት ጥላሁን አስረስ ቻይና ሀገር ውስጥ በነበረው ውድድር ላይ በተካሄደው ምርመራ Triamcinolone acetonide የተባለውን በውድድር ወቅት የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሟ የተረጋገጠ በመሆኑ ለ2 ዓመታት(እ.ኤ.አ ከJune 3/2024-June 2/2026 በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳትሳተፍ ቅጣት ተጥሎባታል፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ማንኛውም አይነት የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት የሚቃወም መሆኑን እያሳወቀ ንፁህ ስፖርትን መሰረት ያደረገ አትሌቲክስ እንዲኖር በማድረግ በጋራ ዶፒንግን እንከላከል በማለት ጥሪውን አስተላልፏል።
ምላሽ ይስጡ