በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት አራት ዓመታት በነበረው ግጭትና በተያያዥ ችግሮች የተነሳ ከ300 ሺሕ ተማሪዎች ውስጥ፣ ከ50 ሺሕ በላይ የሚሆኑት እስከ 2015 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ ወደ ትምህርት ገበታቸዉ ሳይመለሱ መቆየታቸዉ ተገልጿል፡፡
በዚህ መሠረት 82 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በማድረግ የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ መቻሉን የተናገረዉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከ50 ሺሕ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ደግሞ በፀጥታ ችግር ምክንያት በጉልበት ብዝበዛ ሥራ ላይ በሰማራታቸው ትምህርታቸውን ማቆማቸው ተመላክቷል፡፡
በክልሉ ውስጥ በአጠቃላይ 679 የትምህርት ተቋማት መኖራቸውን፣ ከእነዚህ ውስጥም አብዛኞቹ የትምህርት ተቋማት ለተከታታይ ሁለት ዓመታት ክልሉ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ንብረታቸው ወድሟል ፡፡
በተለይ ችግሩ የተከሰተው በመተከልና በካማሺ ዞኖች ውስጥ እንደሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ዘነበ ጠቅሰው፣ በእነዚህ ዞኖችም ሆነ በክልል ደረጃ በአሁኑ ወቅት ሰላም በመስፈኑ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል፡፡ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመንም የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን ከዚህ ቀደም ከነበሩት አመታት የተሻ አፈጻጸም እንዲኖር በትኩረት እየተሰራ ነዉ፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ የትምህርት ገበታቸዉን እየተከታተሉ ያሉ ተማሪዎችን ያነጋገረ ሲሆን ተማሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነ ቀድሞዉንም በክልላቸዉ ያሉት ትምህርት ተቋማት ምቹ ያልሆኑ ካሉበት አከባቢ የሚርቁ እንዲሁም የትምህርት ቁሳቀሱስ ያልተሟሉላቸዉ እንደነበር ነዉ፡፡
ምላሽ ይስጡ