ኅዳር 05 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሰላምን ለማፅናት ያለሙ ሰላማዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው፡፡
ስልፉ እየተካሄደ ያለው በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ቄለም ወለጋ እና የአርሲ ዞኖች ነው፡፡
በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን በሰልፉም በሰላም እጦት ምክንያት የህዝቡ ስቃይ ሊቆም ይገባል፤ ወደ ሰላም መመለስ መሰልጠን ነው የሚሉ መልዕክቶችን እያስተላለፉ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
Leave a Reply