ታኅሳስ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በደብረ ብርሃን ቻይና መጠለያ ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃዮች በቂ የሆነ የምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፎች ባለመደረጉ ተፈናቃዮች ለስደት እየተዳረጉ እንደሆነ ታዉቋል።
በደብረ ብርሃን በተለያዩ ጊዜያትና በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ከሚገኙት መካከል በቻይና ካምፕ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውና ለተከታታይ 4 አመትና ከዛ በላይ የሆናቸው ተፈናቃዮች ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ የቻይና ካምፕ ተፈናቃዮች አብይ ኮሚቴ ፀሃፊ አቶ ንጉሴ ውበቱ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልፀዋል።
በአሁኑ ሰዓት በካምፑ ውስጥ ከ10 ሺህ 170 በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ያሉ ቢሆንም በመንግስት በኩልም ሆነ በተለያዩ ረጂ ተቋማት እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነ አቶ ንጉሱ ተናግረዋል፡፡
በመጠለያ ካምፑ ውስጥ የሚገኙት 10 ሺህ 170 የሚሆኑት በይፋ የሚታወቁት እንጂ፤ በትክክል ቆጠራ ቢካሄድ ወደ 11 ሺህ እንደሚደርስ አመላክተው፤ በመንግስት በኩል የሚደረገው ድጋፍ በ2 ወር አንዳንዴ ደግሞ በ4 ወር ውስጥ ስለሆነ በዚህም ምክኒያት ህጻናት፤ አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን የከፍ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ አቶ ንጉሴ አመላክተዋል፡፡
ለህጻናቱ አልሚ ምግቦች አለመድረሳቸው፤ ለአዋቂዎች ደግሞ አልባሳትና እንዲሁም የመጠለያ ካምፓቸው ከአራት አመት በላይ ስለሆነው ከአካባቢው የአየር ንብረት ጋር ተግዳሮት የፈጠረ እንደሆነም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
አሁን ላይ ለተፈናቃዮቹ የሚደረገው ድጋፍ ሲቀንስ እንዲሁም የተፈናቃዮች ቁጥር ሲጨምር ወጣቶችና እድሜያቸው ለመሰደድ ያልደረሱ ታዳጊዎች በህገ ወጥ መልኩ በመሰደድ ለሞትና ለእስር እየተዳረጉ እንደሚገኙ አቶ ንጉሴ ገልጸዋል፡፡
ባለፈው 2016 ዓ/ም ከ75 በላይ ተፈናቃዮች እንደተሰደዱ ገልጸው በዘንድሮው አመት በትክክል የተጠና ነገር ባይኖርም ቢያንስ ከ150 በላይ የሚሆኑት እንደተሰደዱና በዚህም በፖሊሶች ተይዘው የታሰሩ፤ በሽፍቶች የተገደሉ፤ እንዲሁም ከፍተኛ እንግልት የገጠማቸው እንዳሉም አመላክተዋል፡፡
በክምፑ ውስጥ ካለው ተፈናቃይ አንጻር በመንግስትና በረጅ ድርጅቶች በኩል የሚደረገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ስለቀነሰ መንግስትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ