ታኅሳስ 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከጠቅላላ ጉባዔ፣ ከኦዲትና በሴት አባላት ቁጥር አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋር በተገናኘ 11 ፓርቲዎች ላይ የዕግድ ውሣኔ አሳልፎ የነበረ ቢሆንም ከታህሳስ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የ5 ፓርቲዎችን የማስጠንቀቂያ እግድ ማንሳቱን አሳዉቋል፡፡
የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ በቀዳሚነት ለመታገዱ ምክንያት የነበረው የአባላቱን ፎቶና መታወቂያ በአስቸኳይ እንዲያቀርቡ መጠየቁ እንደነበር የሚናገሩት የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል ሞግዲሶ በአሁኑ ወቅት የማስጠንቀቂያ እገዳው መነሳቱ ለቀጣይ ምርጫ ፓርቲውን ተፎካካሪ የሚደርጉ ስራዎችን ለመስራት እንደሚያስችለዉ ተናግረዋል፡፡
የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ከ4መቶ ሺህ በላይ አባላት እንዳሉት የሚናገሩት ሊቀመንበሩ አባላቱን አሁንም ለማደረጀት እና ትክክለኛው የአባላቱን ቁጥር ለመለየት በሃገሪቱ ላይ ያለው ነባራዊ ሁኔታ አስቻይ እንዳልሆነ እንዲሁም በፓርቲያቸው ውስጥም ሊሻሻሉ የሚገባቸው አስራሮች መኖራቸውን ነው የፓርቲው ሊቀመንበር ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለጹት፡፡
በእቅዳችሁ መሰረት የሴት አባላት ብዛት አላሳወቃችሁም በመባል ታግዶ የነበረው የአገው ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አሁን ላይ እገዳው መነሳቱ ለቀጣዩ ምርጫ ከፍተኛ አስተዋፆ እንደሚኖረው የፓርቲው ሰብሳብ ዶክተር አዲሱ መኮንን ተናግረዋል፡፡ ፓርቲው ከፍተኛ ቁጥር ያለው አባል እንዳለው የሚናገሩት ሰብሳቢው በክልሉ ተንቀሳቅሶ ሰላምን ለማስፈን ለሚሰራው ስራም የማስጠንቀቂያ እግዳው መነሳቱ አስተዋፆ እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እግድ ጥሎባቸዉ ከነበሩ 11 ፓርቲዎች ውስጥ ለ5ቱ ፤ ለዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ ለአዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ ለጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ ለኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ህብረት እና ለአገው ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የማስጠንቀቂያ እግድ ማንሳቱን አስታውቋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ